ስርዐቱ በሚወስደው እጅግ የከፋ የአፈና ተግባር ሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ ምድር አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ ይህ ምንም የሚስተባበል ነገር የለውም የተገለጠ እውነት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ በርካቶች ሰላማዊ ትግል ማድረግ አስቸጋሪ ነው በሚል የትግል ስልት እስከመቀየር ተገደዋል፡፡ እያየን እንዳለነው ስርዐቱ ይህንን ጠንክሮ እየሰራበት ይገኛል፡፡ በሰላም ትግል የወንድ በር ሊሰጡት የሚታገሉትን ንፁሃን እንኳ በሽብር ሺፋን ወደ ማጎሪያው ማውረዱን ከቀን ወደ ቀን አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡
በዚህ የተነሳ ሰላማዊ ትግል ኢትዮጵያ ውስጥ አይሰራም የሚለው ተቀባይነት እንዲያገኝ ስርዐቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደፋ ቀና እያለ ይገኛል፡፡ ስርአቱ ከሚከተለው ከፋፍለህ ግዛ እና ብልጣብልጥነት አንፃር ይህን ቢያደርግ ብዙ የሚደንቅ አይደለም፡፡ ይህ ግን ስርአቱን በሚቃወሙት ሃይሎች ሲሆን ጥያቄን ያጭራል፡፡ እስከሚገባኝም ይህ ማስታወቂያ የሚያስፈልገውም ጉዳይ አልነበረም፡፡ ስርአቱ ይህንን አጥብቆ እየሰራበት ያለ ስለሆነ፡፡
ከፋፋዩ ስርዐት በሰላማዊ ትግል አይወርድም ብለው የሚያምኑ ሃይሎች የመረጡትን የትግል ስልት አከብራለሁ፡፡ ነገር ግን ከነዚህ ወገን በኩል ሰላማዊ ትግል ኢትዮጵያ ውስጥ አያዋጣም ብለው ፕሩፍ ሲያደርጉ እኛም ትጥቅ ትግል እንዲህ እንዲህ ነው ብለን እንዲሁ ሳየሆን መሬት ላይ የሚረግጥ ትንታኔ ማቅረብ አያቅተንም፡፡ ይህ ግን በተጨባጭ ለትግሉ ምን ይጠቅማል ካልን መልሱ ምንም ነው፡፡ ስለዚህም የመረጡትን የትግል ስልት እኛም እንደምናከብረው እነሱም የኛን ያክብሩልን፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ምርጫውን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት ህዝብ የወሰደውን የምርጫ ካርድ እንዲቀድ ተናግረው ነበር፡፡ ይህ በተጨባጭ ከምርጫው ፖለቲካ ውጪ ለሆነ ሃይል ምን እንደሚጠቅም አይገባኝም፡፡ ስርዐቱ በምርጫ አይወርድም፡፡ የሚያካሂደው ምርጫ ቧልት ነው ለማለት ከሆነ ምርጫ ካርድ ቅደዱ የሚያስብለበት ምክንያት ግልፅ አይደለም፡፡ ያላደረጁትን ህዝብ፣ ምርጫ ካርድ እንዲወስድ ያልጎተጎቱትን ህዝብ ምርጫ ካርድህን ቀደህ ጣል ማለት ትርጉሙ ምንም ነው፡፡ በዋነኝነት ማለት ቢያስፈልግ እንኳን ይህን ማለት ያለባቸው ነፍጥ ያነገቡ ሃይሎች ሳይሆኑ ሰማያዊዎች ናቸው፡፡
ምንም አንኳን ብረት ያነገቡ ሃይሎች የሚከተሉት የትግል ስልት ሰላማዊ ትግል ከሚከተሉ ሃይሎች መተጋገዝ ባያስችላቸውም መጠላለፍ የለባቸውም፡፡ ብረት በማንሳት ህይወታቸውን ለመስጠት የተዘጋጁ ሃይሎች እንዳሉ ሁሉ አገር ውስጥም ያለውን ከባድ ሁኔታ ተቋቁመው እየታሰሩ፣እየተገረፉ እንዲሁም ውድ ህይወታቸውን ጭምር ለመስጠት እየታገሉ ያሉ መሆናቸውን መርሳት የለብንም፡፡ ሁላችንም ባመንበትና በፈቀድነው መንገድ እንሂድ እናንተም እንዲያው አይ የእኔን መንገድ ለምን አልተከተልክም ማለት ተገቢ አይደለም፡፡
አሁንም ቢሆን ህዝብን በማደራጀት ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ችግሩ ስርዐቱ ቤት ለቤት ወርዶ የአፈና መዋቅሩን ሲዘረጋ ተቃዋሚዎች ያለምንም ስራ ወደ ምርጫው መግባታቸው፤ ይህንንም ተከትሎ ስርዐቱ ውጤቱን በመጠቅለሉ ሰላማዊ ትግል አብቅቶለታል ሚባለው እያየለ ምምጣቱ ነው፡፡ ይህ የተሳሳተ አተያይ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር በዘንድሮው ምርጫ መሳተፍ የነበረባቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሶስት እስከ አራት የሚበልጡ መሆን አልነበረባቸውም፡፡ አብዛኛዎቹ የመርህ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ የመርህ ፖለቲካ እያራመዱ ቤት ለቤት የደረሰውን የስርዐቱን አፈና ሰብረው ይገባሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ሁሉ ሳያገናዝቡ ሰላማዊ ትግል አብቅቶለታል ማለት ስህተት ነው፡፡
እርግጥ ነው ነባሩ ባህላችን እስኪርቢቶ ከያዘ ሃይል ይልቅ ነፍጥ ያነገበውን እንደሚያጀግንና የተለየ ክብር እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ እውነታው ግን ሰላማዊ ትግልን የመረጡ ሃይሎች ከሌሎች ያነሰ ወኔ አልያም ቁርጠኝነት ስላነሳቸው እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ አሁን በተጨባጭ ያለውን እውነት ካየነው ነፍጥ አንግበናል ከሚሉ ሃሎች ይልቅ የአንድነትና የሰማያዊ አባላት እስሩንም ድብደባውን እየተጋፈጡ ይገኛሉ፡፡ በተጨባጭ አሁን ላለው ትግል አይጠቅምም እንጂ በርካታ ምሳሌዎችን እያነሱ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ስለሆነም እኛም በመንገዳችን እንሂድ እናንተም በመንገዳችሁ ሂዱ፡፡ በመንገዳችን ባንተጋገዝ እንኳ አንጠላለፍ!
ጥሩውን ተመኘሁ!