ምርጫ
97 ከመካሄዱ 3 አመታት ቀደም ብሎ ነበር የቀድሞ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራኖች መካከል ውይይት ተካሂዶ ነበር፡፡ አንድ ምሁር እጁን አውጥቶ ንግግር አደረገ፤ ይህን የተናገረው ምሁር አሁን ስናስተውል የነብይ ያህል ነበር ለማለት ያስደፍራል፡፡ ምሁሩ እንዲህ ነበር ያለው‹‹…አሁን ላይ ወደኋላ ወስጄ እንዲህ አይደለም፤የብሔር ፖለቲካው ያጠፋናል ወደሚለው ክርክር አልሄድም፡፡ ምክንያቱም በጣም ዘግይተናል! በጣም! አሁን ላይ ምንድነው ልናደርግ የምንችለው፤ ኳሷ በርሶ ቁጥጥር ስር ናት፡፡ እኔ ምለው ቅንነት ነው የሚያስፈልገው የሚመስለኝ፡፡ እርሶ ቅን እንዲሆኑ ብቻ ነው የምመኘው፤ በቅንነት እንዲመሩን ብቻ ነው የምመኘው አሁን፤ ምክንያቱም እዚህ አገር ሌላ የመድብለ ፓርቲ ስርዐት ተቋቁሞ እንዳሉት እርሶ ገበሬው ውስጥ ገብቶ ፋይዳ ያለው ለውጥ የሚያመጣ ፓርቲ አይኖርም እርሶ እያሉ፡፡ አይኖርም… እና አሁን ልል የምችለው እኔ እንደትንሽ ትል እዛ ውስጥ እንደሚንከባለል ትንሽ ህዋስ ልል የምችለው እኔ የዝች አገር ዕጣ! በርሶ ቁጥጥር ስር ስላለ ቅንነትዎ እንዳይለን ብቻ ነው ልል የምችለው፤ተስፋ ላደርግ የምችለው…››
ለመግቢያ ያህል የምሁሩን ንግግር ያቀረብኩት ሀሳቤን በደንብ ይገልፅልኛል ከሚል ነው፡፡ ነብይ ነው ወይ የሚያስብለው ምሁር ደጋግሞ ቅንነት ቅንነት ሲል የነበረው ለምን አንደሆነ ብዙዎቻችን እንደጠቅላዩ መስማት የፈለግን አይመስልም፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ በርካታ ነገሮች ተደርገው አልፈዋል፡፡ ቀድሞ ከነበረው ስልጣኔ ሌላ ታሪካችን የጦርነት ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሲጀመር ታሪክን የመተንተን ስልጣን ለፖለቲከኞች ማን እንደሰጣቸው ባላውቅም ፖለቲካውንም የታሪኩን ትንታኔ እራሳቸው በመስጠት ገናና የነበረችን አገር የ100 አመት ታሪክ ነው ያላት እስከማለት የተደረሰበት መንገድ ሁላችንም በቁጭት የሚያንገበግብ ነው፡፡ በዚህ ተጠቃሚው ማን እደሆነ ግራ ያጋባል፡፡
የኢትዮጵያ ፖለቲካም ሆነ ታሪክ እንጥፍጣፊ ቅንነት ቢታከልባቸው ኑሮ አሁን ያሉበት ደረጃ አይደርሱም ነበር፡፡ ከዚህ ውድቀት የሚታደግ ሳይሆን የበዛው ነገር የሚያወሳስብ እንጂ፤ ከላይ እንዳልኩት ከአክሱም ስልጣኔ ወዲህ አብዛኛው ታሪካችን የጦርነት ነው፡፡ ይህ ሲባል በቅኝ ያልተገዛች አገር የሚገጥማትን የቅኝ ገዢዎች ወረራን ለመቋቋም እንዲሁም በውስጥ አንዱ ንጉስ ሌላውን የስልጣን ባላንጣውን ለማስገበር እንዲሁም በሌሎች አገሮች እንደታየው በግዛት አንድነት ወቅት የሚያጋጥሙ ነገሮች ተከስተዋል፡፡ ይህንን እንደወረደ ወስዶ ይህ ብሄር ነው የጨቆነን፣ የእኛ ጥያቂ የመገንጠል ነው፣ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ነው ወ.ዘ.ተ እያሉ ለእኩይ አላማቸው ሲደክሙ አስተውለናል፡፡ ይህም ተሳክቶላቸው ኤርትራን ከእናት አገሯ አስገንጥለው በአምንባገነን መዳፍ ስር አስገብተዋታል፡፡
አንዳንዴ ሳስብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ተከስተው ያለፉ ነገሮች በሌላው አለም የሌሉ እና ያልተደረጉ ተደርገው ሲነዛ እንሰማለን፡፡ ይህ ነው ቅንነት የጎደለው ማለት፡፡ ብዙ ግዜ የሚነሳው የምኒልክ የግዛት አንድነት ዘመቻ ነው፡፡ ይህንን በቅንነት መመልከት የቻለ ሰው የወደፊቱን መንገድ የተቃና ያደርገዋል፡፡ አሁን የተያያዘው ግን ልዩነትን መዝራት ነው፡፡ አልተማሩም እንዳንል? ተምረዋል የስላጣኔና የትምህርት ማማ በሆኑ አገሮች ኑሮአቸውን አድርገዋል፡፡ ግን ይህ ሁሉ ቢሆን ቅንነት ከሌለው ባዶ ነው፡፡ ለዚህ ነው አንዳንዶች ጥርስ የሌለው አንበሳ የሆኑት፡፡ ለዚህ ነው ተምረውና ተመራምረው ዛሬም በአማራ ገዢ መደብ እና በተቀረው የአማራ ህዝብ መካከል ያለውን ልዩነት ለማየት ያልቻሉት፡፡ ለዚህ ነው ምኒልክ ማለት አማራ፤ አማራ ማለት ምኒልክ የሚሉን፡፡ ይህን ነው የትምህርታቸው ትሩፋት…
እርግጥ አሁን የግላቸውን የስልጣን ጥማት ወደ ህዝቡ በማውረድ እንዲህ ሆነናል፤ እንዲህ ተደርገናል በማለት ህልውናቸውን ልዩት በመንዛት አድርገውታል፡፡ ህዝቡ መቼ የስልጣን ባለቤት ሆኖ ያውቃልና ነው? የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነን ህዝብ ለመወንጀል የሚቀርበው ውሃ የማያነሳ ክርክር ሁሌም ይገርመኛል፡፡ የአማራ ህዝብ ምኒልክን መቼ ነው መርጬሃለሁ ብሎ የሾመው? እንዴትስ ሆኖ ነው የአማራ ህዝብ ማለት ምኒልክ የሆነው? በታሪካችን ብዙ መሳሪ ያለው እንዲሁም በርካታ ወታደር ያለው ከሱ ያነሰውን ሲያሸንፍ አንብበናል፡፡ አሁን ላይ ተጋኖ ሲቀርብ ይገርመኛል፡፡ በ20 አመት ውስጥ ቋንቋ ፈጥረው በቋንቋቸው መጠቀም የጀመሩ ይመስል ብዙ ሲነዛ እንሰማለን፡፡ ድምፃዊው ‹‹የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ›› እንዲል በቅንነት ካየነው የኢትዮጵያ ችግር እንደሌሎች አገሮች ውስብስብ አይደለም፡፡ ይህን ይበልጥ ለማወሳሰብ ግን በርካቶች ታጥቀው ተነስተዋል፡፡
አንዳንዶች የደቡብ አፍሪካን ሁኔታ በማስታወስ እንደዛ አይነት ሁኔታ እዚህም እንዲሆን የሚፈልጉ አሉ፡፡ ይህ በራሱ አሁን ካለው እውነት ጋር ፈፅሞ የማይገጥም ነው፡፡ ማንዴላ ይቅር ሲያባብል ሁለቱም አካላት ነበሩ ማለት የሚቻል ይመስለኛል፡፡ በእኛ አገር ያለው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በእኛ አገረ የነበረው አሁንም ያለው የገዢዎች ጭቆና ነው፡፡ ታድያ እንዴት ነው አሁን ላይ ያለውን ህዝብ ምኒልክ ላጠፋው ይቅርታ ጠይቅ ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ሁሉ ፖለቲከኞች በእንዴት አይነት የስልጣን ጥማት ውስጥ ቢገቡ ነው የሚያስብል ነው፡፡ የታሪክ ትንታኔው እና ፖለቲካው ላይ እንጥፍጣፊ ቅንነት እንደሌለ የምንገነዘበው በደቡብ አፍሪቃ በነጮች እንዲሁም በጥቁሮች ላይ ያለውን የሃብት ሁኔታ ስንገነዘብ ነው፡፡ ምንም እንኳን ጥቁሮቹ ነፃነት ቢኖራቸውም አሁንም ድረስ ነጮቹ አብዛኛውን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረው መገኘታቸው ስናስተውል የደቡብ አፍሪካን ሁኔታ ከእኛ ጋር ማነፃፀሩ ፍፁም ስህትት መሆኑን እንረዳለን፡፡ በእኛ አገር 85% ያህሉ ገበሬ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የሸዋም ገበሬ የሚያርሰው እንደጥንቱ በበሬ ነው፡፡ የባሌም ገበሬ የሚያርሰው እንደዛው በበሬ ነው፡፡ ይህን ነው ልሂቃን ነን የሚሉ የየብሄሩ ተወካዮች አይናቸውን ገልጠው በቅንነት ለማየት ያልፈሉት እውነት፡፡ የከተማውን እንተውና በገጠር የሚኖረውን እንያ! ምን እንታዘባለን? አንድ ሰው አይኑን ስለገለጠ ብቻ አያይም፤ እንዲመለከት በቅንነት ልቡንም መክፈት አለበት፡፡ መፅሐፉ ‹‹ታያላችሁ ግን አትመለከቱም›‹ እንዲል የጠፋውም ይህ ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል ያለፉትን ሁለት መንግስታት ጨምሮ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን ከፋፋይ ስርዐት ብናይ የምንረዳው ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡እነዛ ቅንነት የጎደላቸው ልሂቃኖች ለዘመናት ሲሉት የነበረው ዉሃ የማይቋጥር ትንተናቸው አፈር የበላ ይመስለኛል፡፡ የአፄውን ስርአት ብንመለከት እንኳ ከጠላት ጋር ሲዋጉ የነበሩ አርበኞችን አላስተረፋቸውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው በስልጣናቸው ረግተው ለመቀመጥ ይረዳቸው ዘንድ በዙሪያቸው ያሉትን አርበኞች ማስወገድና በምትኩ አድርባዮችን መተካት፡፡ ደርግም ተቃዋሚዎቹን እያሳደደ በመብላት ሰው በላነቱን አሳይቷል፡፡ ይህም ሰው በላነቱ ለራሱ ሰዎች የቀረ አይደለም፡፡ ‹‹አብዮት ልጇን ትበላላች›› እያለ በቁሙ እራሱን እየገዘገዘ ለውድቀት በቃ፡፡ የኢህአዴግም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ፋሽስት ጣልያን ጥሎት የሄደውን ከፋፍለህ ግዛ በማንሳት የበርካታ ዘመናት ታሪክ ያላትን አገር የመቶ አመት እድሜ ያላት በማስመሰል ከዛም በተጨማሪ ቋንቋን መሰረት ባደረገው ፌደራሊዝም አገሪቷን ሸንሽኖ መግዛቱን ቀጥሏል፡፡ ይህም ህዝቡ በአንድነት እንዳይተባባር በማድረግ ሁሌም የጎሪጥ እየተያየ እንዲኖር እነሱም ያለ ምንም ንቅናቄ ለረጂም ጊዜያት በስልጣን ለመቆት በማሰብ የቆሩመት ነው፡፡
ከላይ እንዳልኩት የልሂቃኑ ቅንነት የጎደለው ትንታኔ አፈር የሚበላው በዚህ ዘመን መጥቶ ነው፡፡ ይህም የህወሓት/ኢህአዴግ የ22 አመታት አገዛዝን ስንመለከት ነው፡፡ እኔ በደርግም በንጉሱም ዘመን አልነበርኩም፡፡ ውልደቴም እድገቴም በኢህአዴግ ዘመን ነው፡፡ ያለፉትን 22 አመታት ስገነዘብ ግን የተረዳሁት ልሂቃኑ እንጥፍጣፊ ቅንነት እንደሌላቸው ነው፡፡ ንጉሱ የተቃወማቸውን ለማጥፋት አያመነቱም፡፡ የተቃወማቸውን በዚህ ዘመን ቋንቋ አማራ ስለሆነ ኦሮሞ ስለሆነ ስላልሆነ ሳይሆን ስለተቃወማቸው ብቻ ነው፡፡ ደርግም እንደዛው እንዳሁኑ መንግስት ማታ ገሎ ጥዋት አፈላላጊ ሳይሆን ገድያለሁ ብሎ እንደሚያውጅ ነው፡፡ ወደ እኔ ዘመን ስንመጣ ህወሓት ኢህአዴግ ከእሱ በተቃራኒ መስመር የቆሙትን ለማጥፋትና የሌሎች መቀጣጫ ለማድረግ የሄደበት መንገድ ስናስተውል ምናለ ፖለቲከኞቹ ቅንጣት ታህል ቅንነት አግኝተው ይህን ቢረዱ ብዬ እቆጫለሁ፡፡ በእርግጥ ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን ቅንነቱ ጠፍቶ እንደሆነ እንረዳለን፡፡
የዚህ ዘመን ምሳሌ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ
የወደፊቱን ሁኔታ በማወሳሰብ ለመቀጠል የፈለጉት እነዛ ቅንነት የጎደላቸው የታሪክ ተንታኞችና ፖለቲከኞች የህወሓትን የበላይነት አስመልክተው ቢጠየቁ ለነሱ ህወሓት ማለት የትግራይ ህዝብ፤ የትግራይ ህዝብ ማለት ህወሓት እንደሚሉ ጥርጥር የለውም፡፡ አያድርገውና ህወሓት በዚህ የበላይነቱ 20 አመታት በስልጣን ቢቆይ እነዚህ ቅንነት የጎደላቸው ሰዎች ለአማራ ህዝብ የሰጡትን ስም ለትግራይ ህዝብ ላለመስጠታቸው ምንም ዋስትና የለም፡፡
እርግጥ ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎች በህወሓት እጅ መሆናቸው እሙን ነው፡፡ ያ ማለት ግን የህወሓት የበላይነት አለ ሊያስብል ይችል እንጂ የትግራይ የበላይነት አለ አያስብልም፡፡ ህወሓት ሌላ የትግራይ ህዝብ ሌላ ፡፡ አንድ ቡድን ተነስቶ ይህን ህዝብ እወክላለሁ ስላለ ብቻ ተወካይ አይሆንም፡፡ ወካይስ በምን መንገድ ነው ውክልናውን የሰጠው? የጉልበት አገዛዝ በሰፈነበት እንዲህ አይነት ውክልና የለም፡፡ ሁሉም ነገር በጉልበት ስለሆነ፡፡ ይህንን በቅንነት መሬት ካወረድነው ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ እንደማይመጥንና እንደማይወክል ሁሉ ብአዴንም የአማራን ህዝብ የመምራት ቅንጣት ታህል አቅም የለውም ማለት ነው፡፡ ግን እንወክላለን ይላሉ፡፡ ያው እንዳልነው ሁሉም ነገር በጉልበት ስለሆነ ጉልበት ያለው ወካይ ነኝ ሊል ይችላል፡፡ አውነታው ግን ተቃራኒው ነው፡፡ ሲጀመር ነፃነት ላንዱ ተሰጥቶ ላንዱ የሚነፈግ አይደለም፡፡ በአሁኑ ግዜ በትግራይ ክልል ያሉ ተቃዋሚዎች አንድነትና አረና ናቸው፡፡ መቼም የአብርሃ ደስታን የፌስ ቡክ ግድግዳ የሚያነብ ሰው ከሌሎች አካባቢዎች በከፋ ሁኔታ በትግራይ አፈና እንዳለ ይገነዘባል፡፡ በዚህ አገር እንደምንመለከተው የዚህኛው ወገን የዚያኛው ወገን የሚባል ነገር እንደሌለ ነው፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የደረሰው ዘረፋና ድብደባ በአረናዎችም ላይ ደርሷል፡፡ ለምን? ካልን ከስርዐቱ በተቃርኖ ስለቆሙ ብቻ፡፡
በትግራይ እነ አሰግደ በፈጠሩት ፓርቲ ከሳቸውም አልፎ ልጆቻቸው ምን እንደሆኑ ሰምተናል፡፡ ይህንን እያዩም በቅንነት አይናቸውን መግለጥ አልቻሉም፡፡ ለምን እዚህ ላይ ማተኮር እንደፈለኩ ግልፅ ነው፡፡ እነዛ ቅንነት የጎደላቸው ሰዎች አሁንም ነገር ለማወሳሰብ ወደ ኋላ እንደማይሉ ስለሚታወቅ ነው፡፡ ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ከቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ በፃፈው መፅሐፍ ‹‹ህወሓትና የትግራይ ህዝብ›› በሚል ርዕስ እንዲህ ብሎ ነበር ‹‹አሁን ባለው የኢትዮጵያ አገዛዝ ውስጥ ዋናውን ሥላጣን የጨበጠው ህወሓት መሆኑን መካድ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ሌሎች ብዙም ትርጉም ያለው ሚና እንደማይጫወቱ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ህወሓት ደግሞ እንደስልጣን መሰረት የሚወስደው አፈ-ሙዝን ሲሆን የትግራይንም ህዝብ እንደ መያዣ(hostage) እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ጥቂቶች በጦርነት ወቅት የተከፈለውን መስዋትነት እየመነዘሩ ሥልጣን ላይ መቆየት ይሞክራሉ፡፡ ይኽን እውን ለማድረግ የትግራይን ህዝብ የሥርአቱ ልዩ ተጠቃሚ በማስመሰል ህወሓት ስልጣን ከለቀቀ የሌላ ብሔር ተወላጅ ወንድሞቹ ሊያጠፉት እንደሚነሱበት በማስፈራራት በትግራይ ህዝብና በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አለመተማመን እንዲነግስ ሆን ብሎ የተከለው መርዝ እያፈራለት ይመስለኛል›› ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው የስርዐቱ ሴራ ሲደመር የነዛ ቅንነት የጎደላቸው ፖለቲከኞች እጅ ሲታከልበት የሚፈጥረው ሌላ ተጨማሪ ችግር እንጂ መፍትሄ አይደለም፡፡ ምክንያት ቅንነት ባዶ…
ለማጠቃለል ያህል አሁን ብቅ ያሉ ፖለቲከኞች ሳይቀሩ ለፍረጃቸው ኢህአዴግን ጨምሮ ሶስቱም ስርአታት ስላልተመቿቸው ወደ ምኒልክ ዘመን መመለስ መርጠዋል፡፡ ይህን ፅሁፍ በምፅፍበት ሰአት እንኳ በታሪክ አንድም የሰነድ ማስረጃ እንኳ የሌለው ሃውልት በአኖሌ ተገንብቶ መመረቁ እየተነገረ ነው፡፡ ዘመን ተሸጋሪ ጥላችን ያለምንም ማስረጃ ለመዝራት ይህንን ያህል ሩጫ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ‹‹የመጣነው መንገድ›› ብቻም ሳይሆን የምንሄድበትም መንገድ ያሳዝናል፡፡ ከታሪክ ለመማር ቢሆን እሰየው የሚያስብል ነበር፡፡ ከታሪክ ለመማርና ያለፈውን ስህተት ላለመድገም ሳይሆን ይህ ምስኪን ህዝብ በታሪክ ሂሳብ እንዲያወራርድ እንጂ፡፡ የሰለጠነ አገር መማራቸው የሰጣቸው ይህን ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ቅንጣት ታህል ቅንነት በውስጣቸው ስለሌለው ነው፡፡
የሆነው ሆኖ ሊታወቅ የሚገባው ግን ይህ ትውልድ ሂሳብ እንደማያወራርድ ነው፡፡ በጭራሽ ይህ ትውልድ ባለፈ ታሪክ ሂሳብ አያወራርድም፡፡ እርግጥ ነው በታሪካችን ውስጥ መልካምም ሆነ ስህተት ነገሮች ተሰርተው ይሆናል፡፡ አሁን ያለው ወጣት በዚህ ጊዜ እንዲህ ተደረገ ፣ እንዲህ ሆነ በሚል አሉታዊ ነገር ብቻ ተለጥፎ ወደፊት እንዳይራመድ የሚደረገው የገዢው ፓርቲና የአንዳንድ ተቃዋሚ ተብዬዎች ሴራን ይህ ትውልድ ተቀብሎ ተግባራዊ ያደርጋል ማለት ዘበት ነው፡፡ ወጣቱ ሊያደርግ የሚችለው በታሪካችን ውስጥ ያለፉትን በጎ ነገሮች በመቀበል ፤ በሌላው አንፃር ደግሞ ጥሩ የማይባሉትን እያስተካከልን ወደፊት መሄድ እንጂ ገዢዎቻችንና ቅንነት የጎደላቸው ፖለቲከኞች እንደሚፈልጉት ትላንት ላይ ተለጥፈን የጎሪጥ እየተያየን ምጣችንን ማርዘም አይደለም፡፡

No comments:
Post a Comment