በቀጣይ ወር ለሚካሄደው ምርጫ ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ድራማው ቀጥሏል፡፡ ስለዚህ ምርጫው ብዙም ላለማለት
ለራሴ ቃል ብገባም ለሚካሄደው ሸፍጥ ዝምታን መምረጥ ለሚሰሩት አይን ያወጣ ድርጊት ይሁንታ መስጠት ስለሆነ መፃፌን
እቀጥላለሁ፡፡ ምርጫውን በገለልተኝነት እመራለሁ የሚለው ምርጫ ቦርድ ከታዛቢዎች ምርጫ ጀምሮ ስርዐቱ የፓርቲ
አባላትን እንዲሁም ከተለያዩ ሊጎች ያወጣጣቸውን አባላቱ ሲያስመርጥ ምርጫ ቦርድ ያለምንም ጥያቄ አፅድቆለታል፡፡
ይህ ሁሉ ሆኖ ነበር የስሙን እንኳ እሩብ የማይመዝነው ምርጫ ቦርድ በአንድነትና በመኢአድ የውስጥ ጉዳይ ገብቶ
የፓርቲ መሪ እስከመምረጥ የደረሰው፡፡
ከዚህ ሁላ ሸፍጥ በኋላ ነው እንግዲህ ምርጫ ቦርድ የግንቦቱን ምርጫ ለመታዘብ ከ15 በላይ ሲቪክ ማህበራት የተወጣጡ ባጠቃላይ 40,000 ያህል ታዛቢዎች ምርጫወን ይታዘባሉ የሚለን፡፡ ከ15 በላይ የተባሉት ሲቪክ ማህበራት ምርጫውን የሚታዘቡት ባለ ድርሻ አካላት ነን ከሚል ይመስለኛል፡፡ ሆኖም ግን እኚህ ማህበራት በገቢር በአምስት አመታት ምን ሲሰሩ ቆዩ? ተግባራቸውስ ምን ነበር? እነዚህ ማህበራት ባለፉት አምስት አመታት በአገሪቱ ውስጥ የተካሄዱትን የመብት ጥሰቶች፣እስሮች፣ድብደባዎች፣የንፁሃንን ሞት እንዲሁም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከደጋፊዎቻቸው ጋር ለመገናኘት ከገዢው ፓርቲ የሚደርስባቸውን እንቅፋት፣የአባላቶቻቸውን እስራት፣ስደት፣እንግልት ወ.ዘ.ተ ሁሉ ሲገልፁ ነበር ወይ? ብለን ብንጠይቅ የምናገኘው ምንም ነገር የለም፡፡
እስከሚገባኝ አንድ ሲቪክ ማህበር ህልውናውን የሚያረጋግጠው በሚሰጠው ሰርተፍኬት አልያም ፅ/ቤት ስለከፈተ ሳይሆን የተነሳለት አላማ ነው፡፡ በተግባር መሬት ላይ የሚፈፅመው ነው ህልውናው መሆን ያለበት፡፡ በተለይ በእዝች አገር ሰብአዊና ዴሚክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ የበኩሌን አደርጋለሁ፣ ሂደቱንም እታዘባለሁ የሚል አካል መሬት ላይ የሚታይ ተግባር መፈፀም አለበት፡፡ በአምስት አመታት የነበረውን ሂደት እንደባለ ድርሻ አካል እየተከታተለ የማይዘግብ ነገሮች እንዲለወጡ የበኩሉን ያላደረገ ሲቪክ ማህበር ምርጫውን የሚታዘብበት ምክንያት ከፕሮፓጋንዳ የዘለለ ሚና የለውም፡፡
አንዳንዶች ይህን ማህበር እንወክላለን የሚሉ እንኳን ምርጫን ሊታዘቡ ይቅርና ለሚወክሏቸው የማህበሩ አባላት እንኳ በትክክል መቆም የማይችሉ ደካሞች ናቸው፡፡ በእውነት እነዚህ የሲቪክ ማህበራት ናቸው ወይስ ስርአቱ በጥቃቅንና አነስተኛ ያደራጃቸው ሎሌዎች? ይህን የምለው በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ሳይሆን መሬት ላይ በሚገለጥ ተግባር ነው፡፡ እራሱን ለውደርት አዘጋጅቶ እየተጋ ያለው የፕ/ር መርጋ በቃና ምርጫ ቦርድ ምርጫውን የአፍርካ ህብረትን ጨምሮ ይህን ይህል ሲቪክ ማህበራት ይታዘባሉ የሚለን ትላንት ለሰሩት ሸፍጥና የገዢውን ፓርቲ ህገ አራዊት ተግባር ለመሸፈን ነው፡፡ ለዚህ ነው ምርጫ መካሄዱ ብቻውን ለውጥ ማምጣት ያልቻለው፡፡ ወደፊትም በዚህ መንገድ ለውጥ አያመጣም፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ ለፓርቲ መሪዎችን እስከ መምረጥ የደረሰው ምርጫ ቦርድ ይህን ምርጫ ለመዳኘት ቅንጣት ታህል የሞራል ብቃት እንደሌለው ሁሉ ሲቪክ ማህበራት ናቸው የሚባሉት በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ሎሌዎችም ሆነ ቅልብ የአፍሪካ ህብረት የቱሪስቶች ቡድን ይህን ምርጫ የመታዘብ የሞራልም ሆነ የህግ መሰረት የላቸውም፡፡ እስከሚገባኝ ምርጫው መካሄዱ ብቻውን ምርጫ ነበር አያስብለውም፡፡ አማራጭ የሌለው ምርጫ እንዴት ሆኖ ምርጫ የሚል ስም እንደተሰጠው እራሱ ትንግርት ነው፡፡ ለዚህ ነው ምርጫ መካሄዱን እና የድምፅ አሰጣት ሂደቱን ብቻ በማየት ‹‹ምርጫው ፍትሃዊ እና ሰላማዊ ነበር›› ሊሉ የተዘጋጁ ሲቪክ ማህበራት ነን የሚሉ ነገር ግን በገቢር ተግባራቸው ሌላ የሆነ አካላት ምርጫውን የመታዘብ የሞራልም ሆነ የህግ መሰረት የላቸውም የምለው፡፡
ስለ ምርጫ ስናስብ ዋናው ነገር የምርጫው ሂደት መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ እንደገባኝ ‹‹ምርጫው ፍትሃዊ እና ሰላማዊ ነበር›› ተብሎ የሚወራው ደረቅ ፕሮፓጋንዳ የሚያሳየው የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን ብቻ እንደሆነ ነው፡፡ ምርጫውን የመተንበይ አቅም ያለው ሂደቱ ነው፡፡ ይህም የድምፅ አሰጣጡን ማለትም ከንጋቱ 12፡00 እስከ ምሽቱ 12፡00 ያለው አይደለም፡፡ በአምስት አመት የተካሄደውን እንቅስቃሴ እንጂ! ጋዜጦችን ዘግተህ፣ መፅሄቶችን ዘግተህ፣ የተቃዋሚ አመራሮችን አስረህ፣ የሲቪክ ማህበራቱን የሚያጠፋ አዋጅ አውጀህ፣ተቃዋሚዎች ከደጋፊዎቻቸው ጋር እንኳ በአዳራሽ እንዳይመክሩ አድርገህ ምርጫው ፍትሃዊ እና ሰላማዊ ነበር ማለት ተራ ቧልት ነው፡፡ ባጠቃላይ አማራጮችን አሳጥቶ የሚካሄድ እንኩዋን ምርጫ ለማለት ቀርቶ ምርጫ ነበር ለማለት አያስደፍርም፡፡
አውነት ለመናገር ምርጫውን እንታዘባለን የሚሉ አካላት፤ ቅልብ የአፍሪካ ህብረት የቱሪስቶች ቡድንን ጨምሮ የድምፅ አሰጣጡን እንጂ የምርጫውን ሂደት የት ይነግሩናል፡፡ ከዚህ አንፃር ሂደቱን አጥብቆ እንደመረመረ የሚገመተው የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን ምርጫውን መታዘብ ምንም እርባን እንደሌለው በመገንዘብ ምርጫውን ከመታዘብ እራሱን ማግለሉ፤ ሂደቱ ዝግ የሆነን ምርጫ መታዘብ ትርጉም እንደሌለውም ስላወቁ ነው፡፡ በዛ ላይ ደግሞ ምርጫውን ቢታዘቡ ገዢው ስርዐት እንዳሰማራቸው ታዛቢዎች የድምፅ አሰጣጡን ብቻ ሳይሆን በአምስት አመት ውስጥ የነበረውን ሂደት በድፍረት የሚናገሩ ስለሆኑ አለመኖራቸው ስርዐቱን የሚጠቅም ሲሆን ተቃውሞ ጎራውን እንደሚጎዳ ግልፅ ነው፡፡

ምርጫ ቦርድ ሆይ! ምርጫውን
ይህን
ያህል
ታዛቢዎች
ይታዘባሉ
የምትሉን
ምርጫው
በአምስት
አመታት
ሂደቱ
ምን
ያህል
ዝግ
እንደሆነ
የማናውቅ
ይመስላችኋል?
አማራጮችን
አጥፍቶ
በዚህም
አማራጭ
የማሳጣት
ዘመቻ
ምርጫውን
በገለልተኝነት
እመራለሁ
የሚለው
ምርጫ
ቦርድ
ተሳታፊ
ሆኖ
የፓርቲ
መሪ
መሾም
እንደጀመረ
የኢትዮጵያ
ህዝብ
የማያውቅ
ይመስላችኋል?
እናም
የገዢውን
ፓርቲ
አባላትን
በታዛቢነት
መዝግባችሁ፣ከተለያዩ
ሊጎች
እንዲሁም
ከጥቃቅንና
አነስተኛ
የተወጣጡ
ሎሌዎችን
እንዲሁም
ቅልብ
የአፍሪካ
ህብረት
ቱሪስቶችን
አሰማርታችሁ
ይህንን
ያህል
ታዛቢ
ምናምን
አትበሉ
ይህ
ሂደቱን
ካለመለወጡም
በላይ
ዘመኑንም
የማይመጥን
ቧልት
ነው፡፡
ምርጫ ቦርድ ሆይ! ምርጫውን
ይህን
ያህል
ታዛቢዎች
ይታዘባሉ
የምትሉን
ምርጫው
በአምስት
አመታት
ሂደቱ
ምን
ያህል
ዝግ
እንደሆነ
የማናውቅ
ይመስላችኋል?
አማራጮችን
አጥፍቶ
በዚህም
አማራጭ
የማሳጣት
ዘመቻ
ምርጫውን
በገለልተኝነት
እመራለሁ
የሚለው
ምርጫ
ቦርድ
ተሳታፊ
ሆኖ
የፓርቲ
መሪ
መሾም
እንደጀመረ
የኢትዮጵያ
ህዝብ
የማያውቅ
ይመስላችኋል?
እናም
የገዢውን
ፓርቲ
አባላትን
በታዛቢነት
መዝግባችሁ፣ከተለያዩ
ሊጎች
እንዲሁም
ከጥቃቅንና
አነስተኛ
የተወጣጡ
ሎሌዎችን
እንዲሁም
ቅልብ
የአፍሪካ
ህብረት
ቱሪስቶችን
አሰማርታችሁ
ይህንን
ያህል
ታዛቢ
ምናምን
አትበሉ
ይህ
ሂደቱን
ካለመለወጡም
በላይ
ዘመኑንም
የማይመጥን
ቧልት
ነው፡፡
No comments:
Post a Comment