ለዚህ ፅሁፍ መነሻዬ በውይይት መፅሔት ‹‹የተቃውሞ ፖለቲካ ተስፋ አለው?›› በሚል ርዕስ የቀረበው ፊቸር ነው፡፡ በአዘጋጆቹ ለጥያቄ የቀረቡ ነጥቦች አንዳንዶቹ በተለይም በተቃውሞ ጎራው ላይ
ተደጋግመው የሚነሱም ናቸው፡፡ ወደ መፍትሄው ለመሄድ ግን ከነዚህ ነጥቦች ውጪ የሚሆን አይመስለኝም፡፡ ለዛሬው በተወሰኑት ላይ ብቻ ሃሳቤን እገልፃለሁ፡፡ ተደጋግሞ እንደሚባልው
የፓርቲዎች ቁጥር መብዛት መነጋገሪያ መሆኑ አልቀረም፡፡ 75 የሚጠጉ ፓርቲዎች መኖራቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡ በቅርቡ ምርጫ ቦርድ
14ቱን መሰረዙን ሰምተናል፡፡ እንደኔ የፓርቲዎቹ መኖር ሰርተፍኬቱን
ይዞ ከመቀመጥ ውጪ ከጥቂቶች በስተቀር መሬት ላይ የሚወርድ ስራ የሚሰሩ
አይደሉም፡፡ በዚህ መክንያት በምርጫ ሰሞን እየመጡ ህዝብን ግራ ከማጋባትና
የአሯሯጭነት ሚናቸውን ከመወጣት ውጪ ፋይዳ ያለው ሚና የላቸውም፡፡ ስለሆነም ቁጥራቸው መኖሩ ብቻውን ፓርቲዎቹ
አሉ ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም በተግባር መሬት ላይ የሉምና!
ሌላው የተነሳው የተቋማዊነት
ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ መሬት የሚወርድ ስራ የሚሰሩ የለውጥ ሃይል የሆኑ ፓርቲዎች በፓርቲያቸው ውስጥ የዲሞክራሲ ባህል እና ተጠያቂነትን
የሚያሰፍን አካሄድ መከተል የህልውና ጉዳይም ነው፡፡ የተወሰደው ጊዜ ተወስዶ ጠንካራ ተቋማዊ መሰረት እንዲይዙ ካልተደረገ የተቃውሞ ጎራው ነገ መንግስት ሊሆን የሚያስችለውን አቅም መገንባት አይችልም፡፡
አሁን ያለውን ሁኔታ ምሳሌ ማቅረብ ይቻላል፡፡ በገዢው ፓርቲ በኩል ጥቅምም ሃይልም አለ፡፡ በተቃውሞ ፖለቲካው ውስጥ ይህ የለም፡፡
ለምሳሌ አንድ ግለሰብ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሲሆን እነዚህን ነገሮች ታሳቢ አያደርግም፡፡ ከዚህ ይልቅ የሰማያዊ ፕሮግራሞችን መሰረት አድርጎ ነው አባል የሚሆነው፡፡
በተለያየ ምክንያት ከፓርቲው ሲለቅም የሚያጣው ጥቅምም ሆነ በመልቀቁ ምክንያት የሚደርስበት ጉዳት የለም፡፡
በዚህ የተነሳ በተለይ
በግለሰቦች መካከል የሚነሱ እሰጣገባዎችና ችግሮች ምክንያት ፓርቲዎቹ
ተናከሱ ተብላሉ ሲባል መስማት የተለመደ ነው፡፡ይህ በዋነኝነት የሆነው የውስጠ ዲሞክራሲውን እንደመጨረሻ በማየት ሲሆን ይህ የውስጠ
ዲሞክራሲ መኖር ግን በጠንካራ ዲሲፕሊን ካልታገዘ አንዳለፈው በውስጥ
ያለውን ዲሞክራሲ ያለአግባብ በመጠቀም መካሪ አልባ ፖለቲከኞች ሊፈነጩበትና ትግሉንም የኋሊት ከመውሰድ የሚያግዳቸው
አጥር አይኖርም፡፡ አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ትግሉን ጨምሮ ለብዙ ነገር እንቅፋት የሆነው ተቋም አልባ አገር መያዛችን ነው፡፡ በዚህ
ምክንት አሁን በተቃዋሚነት የሚገኝ ነገ የመንግስት ስልጣን ከመያዙ በፊት በፓርቲው ወስጥ ተቋማዊ መሰረት በመጣል ምሳሌ መሆን አለበት፡፡
ስርዐቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየወሰዳቸው የመጣቸውን የአፈና
እርምጃዎች ተከትሎ የተቃውሞ ጎራውን ትግል እጅግ ፈታኝ አድርጎታል፡፡ ይህ የሚስተባበል ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህ መሆኑ ቢታመንም
ከዚህ ገሸሽ ማለት የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡ ከዛሬው በበለጠ ችግሮች ተደራርበው ይጠብቁ ይሆናል እንጂ ችግሮቹ በራሳቸው መፍትሄ ሆነው አይመጡም፡፡ ከችግሮቹ መፍትሄዎቹን መፈለግ
ግን የለውጥ ሃይሉ ድርሻ ነው፡፡ እዚህ ላይ ያለው አማራጭ ያሉትን
ቀዳዳዎች በመድፍን ወደፊት መጓዝ ነው፡፡ ወደፊት በሚደረጉ የተቃውሞ
ጎራው እንቅስቃሴዎች በተቻለ መጠን ካለፈው በመማር፤ የወደፊቱን አርቆ በመመልከት
በጥልቀት ከተሰራ ተስፋ ያለው ውጤት የማናይበት ምክንያት የለም፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ከሄድን መሬት ላይ ባለተሰራ ነገር ተስፋ የለምና
ተስፋ ሰጪ ነገር አይኖርም፡፡ ይህን የመወሰን ሃይል ያለው ስልጣን
ላይ ያለው አካል ሳሆን ከብዙ ነገር በዘለለ የለውጥ ሃይሉ መሬት ላይ የሚስቀምጣት ተግባር ናት!
‹‹አዎ እንችላለን!›› ክቡር ገና
No comments:
Post a Comment