እስከሚገባኝ ገዢዎቻችን በቀደዱት የምንፈስ ከሆነ
እዛው ከመዳከር ውጪ አዲስ ነገር አንፈጥርም፡፡ ዛሬ ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ትላንት ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊትም ሆነ ስልጣን
ላይ ከተቆናጠጡ በኋላ በተለይ ያለፉትን መንግስታት አስታከው ስርዐቱ የአማራ ህዝብን ከገዢ መደብ ጋር ጨፍልቆ ለፕሮፓጋንዳው አውሎታል፡፡
በዚህም የተነሳ ደሃው ህዝብ በየደረሰበት የጥላቻ ሰለባ ሆኗል፡፡ በዘመነ ስልጣኑ ያለውን ደግሞ ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ከቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ በፃፈው መፅሐፍ ‹‹ህወሓትና የትግራይ ህዝብ›› በሚል ርዕስ የፃፈውን እዚህ ላቅርበው
‹‹አሁን ባለው የኢትዮጵያ አገዛዝ ውስጥ ዋናውን ሥላጣን የጨበጠው ህወሓት መሆኑን
መካድ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ሌሎች ብዙም ትርጉም ያለው ሚና እንደማይጫወቱ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ህወሓት ደግሞ እንደስልጣን
መሰረት የሚወስደው አፈ-ሙዝን ሲሆን የትግራይንም ህዝብ እንደ መያዣ(hostage) እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ጥቂቶች በጦርነት ወቅት
የተከፈለውን መስዋትነት እየመነዘሩ ሥልጣን ላይ መቆየት ይሞክራሉ፡፡ ይኽን እውን ለማድረግ የትግራይን ህዝብ የሥርአቱ ልዩ ተጠቃሚ
በማስመሰል ህወሓት ስልጣን ከለቀቀ የሌላ ብሔር ተወላጅ ወንድሞቹ ሊያጠፉት እንደሚነሱበት በማስፈራራት በትግራይ ህዝብና በሌላው
የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አለመተማመን እንዲነግስ ሆን ብሎ የተከለው መርዝ እያፈራለት ይመስለኛል››
ነገን የተሻለ ለማድረግ ፍላጎቱ ካለን የብሔር
አጥርም ሆነ የፓርቲ አጥር ሊያግደን አይገባም፡፡ ይህን የምለው ለለውጥ ሀይሉ እንጂ ከአጥራቸው ላለመውጣት እራሳቸውን በጥቅምና
በቁስ አምልኮ ምርኮኛ ላረጉት አይደልም፡፡ ስርዐቱን እቃወማለሁ የሚል የትኛውም አካል ቢያንስ ከስርዐቱ አንድ እርምጃ መሻገር ይጠበቅበታል፡፡
ለምሳሌ በጎንደር እና ደባርቅ በተካሄደው ተቃውሞ ተከትሎ ተደረገ በተባለው ነገር የሚነዛው ፕሮፓጋንዳ በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ ከጊዜያዊ የፖለቲካ ስሜት ተሻግረን ካየነው ተጠቃሚ
የሚሆነው ህወሓት ነው፡፡ ለዚህ ነው በመነሻዬ ላይ እነሱ በሚቀዱት የምንፈስ ከሆነ እዛው ከመዳከር ውጪ አዲስ ነገር እንደማይፈጠር
ለመግለፅ የሞከርኩት፡፡
ባንፃሩ ልዩት ሳያግደን ትኩረታችንን በዜግነት
እና በዜግነት ላይ በማድረግ የስርአቱን ሴራ ማሸነፍ እንችላለን፡፡ በዚህም ከእከክልኝ ልከክልህ አገዛዝ በመሻገር በአገራችን የዴሞክራሲ
ስርዐት መሰረት እንዲጣልና ሁላችንንም በዜግነታችን የምታስተናግድ
ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ማድረግ እንችላለን!
አዎ እንችላለን!
ክቡር ገና!
No comments:
Post a Comment